Women’s Participation is a Blueprint for Sustainable Peace!

Op-ED by SIHA

For the past decade, Ethiopia has been experiencing multiple layers of conflicts, which have resulted in severe levels of sexual and gender-based violence (SGBV). The 2018 political transition was followed by incidents of mob violence, communal conflicts, an armed insurgency in Oromia, and a full-fledged civil war in the Tigray region. Although the Tigray war ended with a peace agreement signed by the Ethiopian government and the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) in Pretoria, South Africa, an armed insurgency subsequently escalated in the Amhara region, posing significant human rights challenges. Furthermore, the Zanzibar negotiation between the Ethiopian government and the Oromo Liberation Army (OLA) failed to yield an outcome. It has been widely reported that these conflicts have subjected women to SGBV, displacement, and various other human rights violations.

As observed worldwide, peace efforts have often failed to include a constant target of violence in these conflicts:  young women. On the other hand, their participation in conflict prevention, resolution, and peacebuilding processes could serve as a blueprint for durable peace and stability. In light of this, the Strategic Initiative for Women in the Horn of Africa (SIHA) gathered more than a dozen young women from across Ethiopia in September 2025, representing various grassroots initiatives. The collective has commemorated the UN International Peace Day with a heated discussion on our failures to ensure the inclusion and participation of the most vulnerable sections of our society — young women — in peace processes.

The voices emerging from the workshop affirm that the exclusion of women, particularly younger generations, from conflict resolution and peacebuilding is a direct threat to stability and sustainability. Even though most of the conflicts in Ethiopia victimize young women, the efforts to prevent conflicts, resolve them, and post-conflict peacebuilding processes disregard the participation of young women. To the contrary, backed by empirical research, participants in the SIHA workshop demonstrated that the durability and sustainability of peace processes without women’s participation are unguaranteed.

The Imperative for Inclusion

Women’s participation in the local and national peace agenda is needed not only because they have the right to but also because it is vital to the durability and success of the peace process, as empirical research overwhelmingly supports. Studies show that when women participate in peace processes, the resulting agreement is 20% more likely to last at least 2 years and 35% more likely to last 15 years. Women’s engagement in peace processes also shifts the dynamics of peace talks, broadening the issues discussed to include human rights, justice, and the root causes of conflict, which are imperative for building community buy-in and a robust, lasting peace that provides for accountability. Furthermore, higher levels of gender equality are statistically associated with a lower propensity for conflict, both within and between states.

Furthermore, the UN Security Council’s Resolutions 2250 (2015), 2419 (2018), and 2535 (2020) together constitute the Youth, Peace, and Security (YPS) agenda. These resolutions explain why youth participation is necessary, including changing the image of youth from perpetrators or victims to change-makers, and ensuring the inclusion of often-disregarded sections of society. Youth participation in peace processes has also yielded results. For instance, youth in Somalia acted as peacebuilding intermediaries, bridging clan lines to foster cooperation and reduce conflict. Projects, like the conflict monitoring network in Sudan, demonstrate the youth’s role in preventing, mitigating, and managing conflicts, as well as in post-conflict peacebuilding.

The Challenge of Tokenism

The collective experience of young Ethiopian women in peace and conflict spaces reveals critical systemic barriers that prevent their full and effective participation, directly undermining the goals of sustainable peace. These observations are strongly corroborated by established international research on the Women, Peace, and Security (WPS) agenda.

A primary challenge identified by young women is that formal inclusion remains largely “quota-oriented and ceremonial.” This finding confirms that despite global commitments, women’s official participation is often “more symbolic than substantive,” severely limiting their capacity to influence core negotiation outcomes. According to research, in 2022, women represented only 16 percent of negotiators in active peace processes. Women constituted, on average, 13 percent of negotiators and 6 percent of signatories between 1992 and 2019. In Ethiopia, too, no women have been represented in the aforementioned Pretoria agreement. Similarly, the failed peace negotiations between the Ethiopian government and the OLA in Zanzibar did not represent women on either side. Could this be the reason the former agreement is waning, while the latter was unsuccessful? The answer may not be a straight yes or no, but it is undoubtedly a contributing factor.

Even in circumstances where women are represented in local peace conferences and platforms, young women noted a failure of inclusive practice, observing that “young women are often missing” and that “there is a lack of intersectionality.” While the foundational frameworks of the WPS (UNSCR 1325) and YPS agendas exist, youth and marginalized groups, including women with disabilities and internally displaced women, are systematically constrained. This exclusion is often rooted in “long-standing cultural norms of exclusion” and exacerbated by a lack of dedicated funding and resources to enable robust involvement by the most vulnerable and marginalized sectors of society.

A damaging perception barrier also hinders young women’s participation in peace processes. Young women noted they are often viewed as “troublemakers rather than peacemakers” by those holding power. This deeply rooted issue stems from an “erroneous view of youth as a threat” to political stability, rather than recognizing them as agents of peace and change. This negative bias from the state and other peace actors limits trust, denies young women access to decision-making platforms, and ultimately diminishes their agency.

Finally, the critique extends to implementation, where participants observe that “the UN’s four pillars in peace… are not considered.” Despite the comprehensive framework provided by UNSCR 1325 (Participation, Protection, Prevention, and Relief/Recovery), peace agreements continue to fall short. Research shows that globally, only about one-third of peace agreements include specific provisions addressing the unique needs and rights of women and girls, confirming a persistent gap between high-level policy commitments and gender-responsive outcomes on the ground.

The Road to Peace and Stability

The solutions proposed by the young women constitute a transformative approach, focusing on legal, institutional, and grassroots shifts. Their primary recommendation is for a comprehensive legal and policy mandate to ensure women’s participation in peace processes. The women’s rights defenders unanimously agree that it is imperative to have a clear, assertive legal framework that is consistent with UN recommendations to strengthen the gender-responsive language and legal validity of peace provisions.

The framework for women’s participation should emphasize leveraging creative means, such as digital spaces, the arts, and cultural platforms, as well as traditional institutions (such as Sinqee among Oromo women) and other grassroots initiatives to build peace bottom-up.  Academic findings also reaffirm that women’s informal peacebuilding activities at the local level have a transformative impact when formal talks stall.

Women’s inclusion must also go hand in hand with their empowerment; however, the challenge persists that capacity-building efforts are treated as a one-time training issue. The cohort of young women strongly asserted that capacity-building activities should be continuous and incremental. It is a strategic recognition that women must be prepared and sustained to wield influence, moving beyond simple numerical and ceremonial representation to meaningful participation.

To narrow the generational gap, they recommend creating and promoting dedicated platforms for intergenerational dialogue, which directly address documented barriers to trust and effective collaboration across age divides.

By addressing these recommendations, policymakers and stakeholders can leverage the unique insights of young women, ensuring that peace processes are comprehensive, address root causes, and build the societal buy-in necessary for genuine, long-term stability.

 

ለዘላቂ ሰላም የሴቶች ተሳትፎ ቅድመ ሁኔታ ነው!

የሲሃ አስተያየት

ኢትዮጵያ ላለፉት ዐሥርት ዓመታት በርካታ ግጭቶችን እያስተናገደች ነው፤ይህም ከፍተኛ የሆነ ጾታዊ እና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን አስከትሏል። በ2010 የተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ የደቦ ፍርድንና የእርስ በርስ ግጭቶችን ጨምሮ በኦሮሚያ የታጠቁ አማፂያን እንቅስቃሴን፣ እንዲሁም በትግራይ የተካሔደውን የእርስ በርስ ጦርነት አስከትሏል። የትግራይ ጦርነት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በተፈራረሙት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ቢጠናቀቅም፣ በአማራ ክልል የታጠቁ አማፂያን የትጥቅ እንቅስቃሴ ከዚያ በኋላ እንዲጀምሩና የሰብዓዊ መብቶች ተግዳሮቱ አሁንም እንዲቀጥሉ ሰበብ ሆኗል። በተጨማሪም ዛንዚባር ውስጥ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የተደረገው ድርድር ውጤት ማምጣት አልቻለም። እነዚህ ግጭቶች በተለይ ሴቶችን ለጾታ እና ጾታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች፣ መፈናቀሎች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መዳረጋቸው በሰፊው ተዘግቧል።

በዓለም ዙሪያ እንደተስተዋለው፣ ወጣት ሴቶች በግጭቶች ውስጥ ሁሉ ቋሚ የጥቃት ዒላማ ናቸው። ይሁን እንጂ፣ በግጭት መከላከል፣ አፈታት እና ሰላም ግንባታ ሒደት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እምብዛም ነው። የሴቶች ተሳትፎ፣ በጥቅሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር እንደ ቅድመ ሁኔታ ሊቆጠር ይችላል። በሰላም ሒደቶች ውስጥ የወጣት ሴቶች ተሳትፎን በተመለከተ፣ የአፍሪካ ቀንድ ሴቶች ስትራቴጅክ ኢኒሼቲቭ (ሲሃ) በመስከረም ወር 2018፣ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ወጣት ሴቶችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። ውይይቱ የተዘጋጀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም ዐቀፍ የሰላም ቀንን በማስመልከት ሲሆን፣ የወጣት ሴቶችን ተሳትፎ በሚገድቡ ተግዳሮቶች ላይ  የጦፈ ውይይት ተደርጎበታል።

ከውይይቱ የተገኙት ድምጾች እንደሚያመለክቱት፣ ሴቶች በተለይም ወጣት ሴቶች ከግጭት አፈታት እና ሰላም ግንባታ መገለላቸው፣ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት ቀጥተኛ ተግዳሮት መሆኑን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል። የተሳታፊዎቹ አስተያየትም፣ ከብዙ የምርምር ሥራዎች ግኝት ጋር የሚጣጣም ነው። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹ ግጭቶች ወጣት ሴቶችን የጥቃት ኢላማ የሚያደርጉ ቢሆንም ግጭቶችን ለመከላከል፣ ለመፍታት እና ከግጭት በኋላ የሚከሰቱ የሰላም ግንባታ ሒደቶች ውስጥ ወጣት ሴቶችን ለማሳተፍ ቸልተኝነት ይስተዋላል።

ወጣት ሴቶችን የማካተት አስፈላጊነት

ሴቶችን በአካባቢያዊ እና በአገር ዐቀፍ የሰላም አጀንዳዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ የሚያስፈልገው መብት ስላላቸው ብቻ ሳይሆን ለሰላሙ ዘላቂነት እና ስኬት ወሳኝ በመሆኑም ጭምር ነው። ይህ ድምዳሜ በተጨባጭ ጥናትና ምርምሮች የተደገፈ ነው። በርካታ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሴቶች በሰላም ድርድር ውስጥ ሲሳተፉ የሚገኘው የሰላም ስምምነት ቢያንስ ለሁለት ዓመታት የመዝለቅ 20 በመቶ የበለጠ ዕድል እና ለ15 ዓመታት የመቆየት 35% ሴቶችን ከማያሳትፈው ስምምነት የበለጠ ዕድል አለው። የሴቶች በሰላም ሂደት ውስጥ መሳተፍ የሰላም ድርድሮችን ተለዋዋጭነት በማገናዘብ፣ የድርድሮቹን ነጥቦች አድማስ በማስፋት ሰብአዊ መብቶችን፣ ፍትህን እና የግጭት መንስኤዎችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አንቀፆችን በድርድሮቹ ሰነዶች ውስጥ በማካተት፣ የስምምነቱን ማኅበረሰባዊ ተቀባይነት በማሳደግና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር አስፈላጊ ሁነው በጥናቶች ተለይተዋል። በተጨማሪም፣ ከፍ ያለ የፆታ እኩልነት ደረጃዎች ያሉባቸው ኅብረተሰቦች በጥቅሉ ለግጭት የመጋለጥ ዝንባሌያቸው ዝቅተኛ ነው

 የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች 2250 (2015)፣ 2419 (2018) እና 2535 (2020) የወጣቶች፣ የሰላም እና ደህንነት አጀንዳዎች የሚባሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አስተዋውቀዋል። እነዚህ የውሳኔ ሐሳቦች የወጣቶች ተሳትፎ ለምን እንደሚያስፈልግ ያብራራሉ፤ ይህም የወጣቶችን ገጽታ ከአጥፊነት ወይም ተጠቂነት ወደ ለውጥ አምጪነት መለወጥን ጨምሮ ብዙ ጊዜ በሰላም ሒደቶች ውስጥ የማይካተቱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማካተትን አስፈላጊነትን ይጠቅሳል። በሰላም ግንባታ ሒደቶች ውስጥ የወጣቶች ተሳትፎ ውጤት እንደሚያስመዘግብ በተግባርም ታይቷል። ለምሳሌ፣ የሶማሊያ ወጣቶች እንደ ሰላም ግንባታ አማላጅ በመሆን፣ ትብብርን ለመፍጠር እና ግጭትን ለመቀነስ ጎሳዎችን እርስበርስ በማገናኘት አገልግለዋል። የሱዳን ወጣቶች የግጭት ሁኔታ መከታተያ ኔትወርክ በማቋቋም፣ ግጭቶችን በመከላከል፣ በመፍታት እንዲሁም ከግጭት በኋላ የሰላም ግንባታ ላይ፣ ድጋፍ ከተደረገላቸው የወጣቶች ሚና ጉልህ እንደሆነ ማሳየት ችለዋል።

ከነቢብ ወደ ገቢር

ወጣት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ግጭትን በተመለከተ ያለፉበት የጋራ ተሞክሮ፣ ሙሉ እና ውጤታማ ተሳትፏቸውን የሚከለክሉ እና የዘላቂ ሰላም ግቦችን በቀጥታ የሚያናጉ ወሳኝ የስርአት መሰናክሎች እንዳሉባቸው ያሳያል። እነዚህ ተግዳሮቶች በሌላውም ዓለም የተስተዋሉ እንደሆኑ፣ በሴቶች፣ ሰላም እና ደኅንነት አጀንዳ ላይ በተቋቋሙ ዓለም ዐቀፍ ጥናቶች ላይ ተመላክቷል።

በወጣት ሴቶች ተሳትፎ ጉዳይ ተቀዳሚው ተግዳሮት፣ ተሳትፎ አለመኖሩ ሲሆን፣ አልፎ አልፎ ሴቶች ለተሳትፎ በሚታጩበት ጊዜም ቢሆን “ኮታ-ተኮር እና የይስሙላ (ትዕምርታዊ)” ሆኖ መቆየቱ ሌላኛው ነው። የይስሙላ ተሳትፎም ቢሆን፣ ከወጣት ሴቶች ይልቅ፣ በእድሜ የገፉ ሴቶችን የሚወክልበት ዕድል ሰፊ ነው። ምንም እንኳን በሴቶች ተሳትፎ ማነስ ጉዳይ ዓለም ዐቀፋዊ መግባባት እና ስምምነት ቢኖርም፣ አፈፃፀሙ ላይ ግን ቁርጠኝነት የለም።  

ሴቶች የሚወከሉበት የሰላም ስምምነት፣ ከማይወከሉበት ይልቅ ውጤታማነቱ በጥናት ቢረጋገጥም፣ አሁንም ድረስ ውክልናቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው። እኤአ በ2022 ይፋ በሆነ ጥናት ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሴቶች ትርጉም ያለው ውክልና የነበራቸው እና ንቁ ተሳትፎ ያደረጉባቸው የሰላም ሂደቶች ከጠቅላላው 16 በመቶውን ብቻ ይወክላል። እኤአ ከ1992 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ ሴቶች በአማካይ 13 በመቶ የሰላም ድርድሮች ውስጥ ተደራዳሪዎች ተደርገው ሲሰየሙ፣ 6 በመቶዎቹ ውስጥ ብቻ የሰላም ድርድሩ ፈራሚዎች ሆነዋል። በኢትዮጵያም ከላይ የተጠቀሰው የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ አንድም ሴት በተደራዳሪነትም ይሁን በስምምነቱ ፈራሚ ሆና አልተወከለችም። በተመሳሳይ፣ ዛንዚባር ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተደረገውና የከሸፈው የሰላም ድርድር በሁለቱም ወገን ሴቶች አልተወከሉበትም። በዚህ መንገድ የተገኘው የሰላም ስምምነትም፣ የመጀምሪያው ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ሲሆን፣ ሁለተኛው ግን ጭራሹኑ አልተሳካም፤ ለዚህ ምክንያቱ የሴቶች ተሳትፎ አለመኖር ይሆን የሚል ጥያቂ ቢነሳ፣ መልሱ ቀጥተኛ አዎ ወይም አይደለም ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን የሴቶች ተሳትፎ አለመኖሩ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አያጠራጥርም።

ሴቶች በአካባቢያዊ ጉዳዮች በሚደረጉ የሰላም ኮንፈረንሶች እና መድረኮች ላይ የሚወከሉበት ጊዜ ሲኖር እንኳን “ወጣት ሴቶች ብዙ ጊዜ አይወከሉም” ሲሉ ወጣቶቹ ሴቶች ቅሬታቸውን አንስተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ሰላምና መረጋጋት (UNSCR 1325) እንዲሁም የወጣቶች የሰላምና ደህንነት አጀንዳዎች መሰረታዊ ማዕቀፎች ቢኖሩም፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኛ ሴቶችን እና ከቅዬአቸው የተፈናቀሉ ሴቶችን ጨምሮ፣ የሌሎችም ግፉዓን የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ስልታዊ በሆነ መልኩ የተገደቡ ናቸው። ይህ ዓይነቱ ማግለል ብዙውን ጊዜ “ለረጅም ጊዜ ከዘለቀው አግላይ ባሕላዊ ደንቦች” የሚቀዳ ነው። ግፉዓን፣ የጥቃት ተጋላጭ እና የተገለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጠንካራ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሃብትና ድጋፍ እጥረት መኖሩ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል።

ጎጂ አመለካከቶች ወጣት ሴቶችን በሰላማዊ ሂደት ውስጥ እንዳይሳተፉ ሌላው ተግዳሮት ሆኖባቸዋል። ወጣት ሴቶች በሥልጣን ላይ ባሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ እንደ “ችግር ፈጣሪዎች” ተደርገው እንደሚታዩ ተናግረዋል። ይህ ስር የሰደደው ጎጂ አመለካከት፣ ወጣቱን የሰላምና የለውጥ ፈላጊ አድርጎ ከመቀበል ይልቅ ለፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንደ ስጋት አድርጎ ከመመልከት አባዜ የመነጨ ነው። ይህ ከመንግሥት እና ከሌሎች የሰላም ተዋናዮች የሚመነጭ አሉታዊ አመለካከት፣ ወጣት ሴቶችን የውሳኔ ሰጪ መድረኮች ላይ እንዳይገኙ እንቅፋት ከመሆኑም ባሻገር ውክልናቸውን ይቀንሳል።

የወጣት ሴቶች ተሳትፎ አለመኖር ጉዳይ “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ዋልታዎችንም” ጭምር ከግምት ውስጥ እንዳይገቡ እንዳደረጋቸው ወጣቶቹ ሴቶች በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል።  የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ሰላምና መረጋጋት አጀንዳ 1325  የሰላም ዋልታዎች የሚላቸው ተሳትፎ፣ ጥበቃ፣ መከላከል፣ እና እፎይታ/ማገገሚያ፣ አጠቃላይ ማዕቀፍ ቢኖረውም ቅሉ፣ የሰላም ስምምነቶች ግን እነዚህን ከግምት ውስጥ ያስገቡ አይደሉም። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ፣ ከሰላም ስምምነቶች ውስጥ አንድ ሦስተኛው ብቻ የሴቶች እና ልጃገረዶች ልዩ ፍላጎቶችን እና መብቶችን የሚመለከቱ ልዩ ድንጋጌዎችን የሚያካትቱ ናቸው። ሌሎቹ በከፍተኛ ደረጃ የፖሊሲ ቁርጠኝነት እና ሥርዓተ-ፆታ አገናዛቢነት የሚጎድላቸው ናቸው።

የሰላም እና የመረጋጋት መንገድ

በወጣቶቹ ሴቶች ያቀረቧቸው የመፍትሔ ሃሳቦች በሕጋዊ፣ ተቋማዊ እና መሠረታዊ ለውጥ ላይ ያተኮረ ሥራን አስፈላጊነትን ያመለክታል። ዋና ዋና ምክረ ሐሳቦቻቸው የሴቶችን በሰላማዊ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ የማድረግና የመወከል መብት እና ዕድል ለማረጋገጥ ሁሉን ዐቀፍ የሕግ እና የፖሊሲ ውሳኔዎች እንዲኖሩ ያስፈልጋል። የሴቶች መብቶች ተሟጋቾቹ፣ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እና ሴቶች፣ በተለይም ወጣት ሴቶች በሰላም ሒደት ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥቆማዎች መሠረት፣ ሥርዓተ ፆታ አገናዛቢ፣ ግልጽ እና ቁርጠኛ የሕግ እና ፖሊሲ ማዕቀፎች መኖር አለባቸው። 

የሴቶች ተሳትፎ ማዕቀፍ እንደ ዲጂታል ምኅዳሮችን፣ የኪነ-ጥበባት እና የባሕል መድረኮችን እንዲሁም ባሕላዊ ተቋማትን (ለምሳሌ በኦሮሞ ሴቶች መካከል እንደ ሲቄ ያሉ ተቋማትን) እና ሌሎች ሰላምን ከታች ከብዙኃን ወደ ላይ ለመገንባት የሚረዱ ዘዴዎችን መጠቀም ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል። ጥናታዊ ግኝቶችም መደበኛ ድርድሮች ሲቆሙ እና ለውጥ ማምጣት ሲሳናቸው፣ የሴቶች መደበኛ ያልሆነ የሰላም ግንባታ እንቅስቃሴዎች  ሰላም ለማምጣት እንደቻሉ በማሳያዎች ያረጋግጣሉ።

የሴቶች ተሳትፎ ለይስሙላ እና ለትዕምርት ሳይሆን፣ ትርጉም ያለው እና ከሙሉ የውክልና ሥልጣን ጋር መሆን አለበት። ሆኖም ሴቶች በተለያዩ ተግዳሮቶች ሳቢያ የአቅም ውሱንነቶች ሊኖሩባቸው ይችላሉ፤ ስለሆነም የአቅም ግንባታ ሥራዎች እንደ አንድ ጊዜ የሥልጠና ጉዳይ ሳይሆን በዘላቂነት እና በተከታታይነት ሊመቻቹላቸው ይገባል። የሴቶች ተሳትፎና ውክልና ከቀላል የኮታ ብቻ ውክልና ወደ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ሊሸጋገር የሚችለው፣ ሴቶች ተዘጋጅተው እና በሙሉ አቅም እንዲሳተፉ ማድረግ ሲቻል እንደሆነ ወጣቶቹ ተወያዮች አበክረው ተናግረዋል።

የትውልድ ክፍተት ሌላው ችግር ነው። ይህንን ለማጥበብ፣ የበይነ ትውልድ ውይይቶችን ለማድረግ የተነደፉ መድረኮችን መፍጠር እና ማመቻቸት ያስፈልጋል። ይህም በወጣት እና ጉምቱ ሴቶች መካክል ያለውን የመተማመን እና ውጤታማ ትብብርን ያሳልጣል።

እነዚህን የለውጥ ምክረ ሐሳቦች በማስተናገድ፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ባለድርሻ አካላት የወጣት ሴቶችን ልዩ አቅም መጠቀም፣ የሰላም ሒደቶች ሁሉን አሳታፊ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ መሠረታዊ ተግዳርቶቶችን መቅረፍ እና ለእውነተኛ እና ዘላቂ፣ ሰላምና መረጋጋት አስፈላጊ የሆነውን የኅበረተሰብ አመኔታ መግዛት ይችላሉ።